Fana: At a Speed of Life!

ቆቦ ወደ ቀድሞ ሠላማዊ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ከአሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል ነጻ የወጣችው የቆቦ ከተማ ወደ ቀድሞ ሠላማዊ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ።

የሽብር ቡድኑ በአማራና በአፋር ክልል አካባቢዎች በቆየባቸው ጊዜያት በዜጎች ላይ ሠብዓዊ፣ ማኅበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳቶችን አድርሷል።
የቆቦ ከተማም የተጠቀሱት ጉዳቶች ከደረሱባቸው አካባቢዎች መካከል ትጠቀሳለች።

እንደ ከተማዋ ነዋሪዎች ገለጻ፥ በቤተ-እምነቶች የኃይማኖት አባቶችን በማስገደድ “በኅብረተሰቡ ውስጥ ያላችሁን ተሰሚነት ተጠቅማችሁ ጥሩ ሰው ናቸው ብላችሁ መስክሩ” እያሉ ከፍተኛ ማንገላታትና ጫና ሲያደርጉ ነበር።

የሽብር ቡድኑ ወራሪዎች የኃይማኖት ተቋማት ንብረቶችን በማስወጣት ቤተ-እምነቶችን የከባድ መሳሪያ ምሽግ አድርገው መጠቀማቸውንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

የወገን ጦር በሽብር ቡድኑ ወራሪ ላይ ድል ከተቀዳጀ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞ ሠላማዊ የሥራ እንቅስቃሴ እየተመለሰች ነው ሲሉም ገልጸዋል ነዋሪዎቹ።

አርሶ አደሩ የእርሻና የመኸር ሥራውን፣ የከተማው ነዋሪም የንግድ ሥራውን እየከወኑ ነው ብለዋል።

ነዋሪዎቹ የሽብር ቡድኑ በከተማዋ የመንግስትና የግል ድርጅቶች ላይ ጭምር ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት ማድረሱን ፤ በርካታ ዜጎችም ለሠብዓዊ ቀውስ መዳረጋቸውን ገልጸዋል።

ያለው ለሌለው እያካፈለ የቆየ ቢሆንም አሁን መንግስት፣ ግብረሰናይ ድርጅቶችና በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመለየት የጤና እና የሠብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

በከተማዋ የትራንስፖርት አገልግሎትን ጨምሮ ሱቆች ምግብ ቤቶችና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎት መስጫዎች ስራ እየጀመሩ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.