Fana: At a Speed of Life!

ቋሚ ኮሚቴው የባለስልጣኑን የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና፣ አርብቶ አደርና አየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንን የ2013 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ገምግሟል፡፡

አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ከማድረግ አንጻር የቡና ጣዕም ውድድር በሃገሪቱ መዘጋጀቱ ከገጽታ ግንባታ፣ የአርሶ አደሮችን ጥቅም ከማስጠበቅ አንጻር እንዲሁም ጥራት ያለው ቡና አዘጋጅቶ ሌሎች አሸናፊ የሚሆኑ አርሶ አደሮችን ከማፍራት አንጻር ድርሻው የጎላ መሆኑ ተገምግሟል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ የገበያ መረጃ መቆጣጠሪያ ስርዓት ተግባራዊ የሚደረግበት ሶፍትዌር እንዲበለጽግ መደረጉ ትልቅ እርምጃ መሆኑም ተነስቷል፡፡

የሃገሪቱን ቡና ለመላው ዓለም ሊያስተዋውቅ የሚያስችለው መለያ መዘጋጀቱና በተለያዩ ሃገራት እንዲመዘገብ የማስደረጉ ስራ መጀመሩ አበረታች እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን የግብይት መዳረሻዎችን ከማስፋት፣ ስፔሻሊቲ ቡና ላይ የማተኮር እና ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት የተሄደበት ርቀት አበረታች እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በቂ የቡና ባለሙያ ከማፍራት አንጻር በዲላ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት እየተሰጠ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፥ ከሚዛን ቴፒ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ሁለገብ የቡና እና ቅመማ ቅመም ስልጠና ስርአተ ትምህርት ተዘጋጅቶ ባለሙያዎችን ለማሰልጠን የስምምነት ሰነድ ተፈርሟል ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም ደረጃውን የጠበቀ የቡና ቅምሻ ስልጠና ማዕከል እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቡና ቅምሻ ላቦራቶሪ ተገንብቶ ለትግበራ እየተዘጋጀ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.