Fana: At a Speed of Life!

ቋሚ ኮሚቴው የኮሚሽኑን የኮቪድ-19 የመከላከል ምላሽ አበረታታ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 22 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶች እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የኮቪድ-19 ወረርሺኝን ለመከላከል ያደረገውን ምላሽ አበረታታ፡፡
ቋሚ ኮሚቴው ሰሞኑን በኮሚሽኑ ባካሄደው የመስክ ምልከታ÷ ኮሚሽኑ የኮቪድ-19ን ተፅዕኖ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ለመመለስ ያሳየውን ቁርጠኛነት እና ቀጣይ አካሄዱን ለመለየት መነሻ ጥናት ማካሄዱን በጥንካሬ ገምግሟል፡፡
ኮሚሽኑ የኮቪድ-19 ወረርሺኝን ተፅዕኖ ተቋቁሞ የስፖርቱን ዘርፍ መልሶ ለማቋቋም ያደረገውን ጥረት በሌሎች ተግባራትም በመድገም ለስፖርቱ ሁለንተናዊ ዕድገት መሥራት እንዳለበትም አሳስቧል፡፡
ኮሚሽኑ የእግር ኳስን እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዲሁም 30 የሚሆኑ የስፖርት ማኅበራትን የመከታተል፣ የመደገፍ እና የመቆጣጠር ኃላፊነት ያለበት ሲሆን÷ የክልል አደረጃጀቶችን ጭምር በማሳተፍ በኮቪድ ዙሪያ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ማካሄዱ ሊቀጥል የሚገባ ተግባር መሆኑንም ኮሚቴው ማመላከቱን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.