Fana: At a Speed of Life!

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ታላቅ የኢፍጣር መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀላባ ቁሊቶ ከተማ በሺህዎች የሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ደማቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር መሀመድ ኑርዬ እና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከንቲባ አቶ ሃሩና አሕመድን ጨምሮ የዞን እና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም በርካታ የእስልምና እና የክርስትና እምነት ተከታዮች ተሳትፈዋል።
የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር መሀመድ ኑርዬ በመርሐ ግብሩ ባደረጉት ንግግር÷ የረመዳን ወር የአንድነትና የመተሳሰብ ወር በመሆኑ አቅመ ደካሞችን መደገፍ አለብን ብለዋል።
የረመዳን ወር የመቻቻል፣ የመከባበርና የአንድነት ወር በመሆኑ÷ ሕዝበ ሙስሊሙ አንድነቱን ማጠናከር እንዳለበት እና ይህን በጎ ወር ለጥሩ ነገር መጠቀም እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከንቲባ አቶ ሃሩና አሕመድ÷ ይህን ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በጥላሁን ይልማ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.