Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል “ስለ አባይ እሮጣለሁ”  የጎዳና ላይ የሩጫ  ውድድር ተካሄደ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀረር ከተማ ከጨለንቆ  አደባባይ  እስከ ራስ  መኮንን  አደባባይ  “ስለ አባይ እሮጣለሁ” የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሄደ፡፡

የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትና  የክልሉ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በጋራ ያዘጋጁት  ውድድር ነው።

በውድድሩ በሁለቱም  ፆታዎች  ሦስት  መቶ የሚጠጉ ተሳታፊዎች  “ግድቡ የኔ ነው” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን በመያዝ ተሳትፈውበታል።

የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ  ሄኖክ ሙሉነህ ፥ የህዳሴው ዋንጫ አሁን ላይ በሀረሪ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች እየተዘዋወረ መሆኑን ገልጸው  እስካሁን   ከስድስት ወረዳዎች ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።

ስለ አባይ እሮጣለሁ በሚል የተዘጋጀው የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ዓላምም ለግድቡ የሚደረገውን ድጋፍ ለማጠናከር ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በውድድሩ ተሳትፈው አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች የዋንጫ ሽልማትም ከዕለቱ የክብር እንግዶች ተበርክቶላቸዋል።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.