Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል የተካሄደው ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊና ገለልተኛ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 3፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የሀረሪ ክልል የተፎካካሪ ፖርቲዎች የጋራ ምክርቤት በክልሉ መስረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም የተካሄደውን ምርጫ ተንተርሶ መግለጫ አዉጥቷል።
ምክርቤቱ በመግለጫው ትላንትና በምርጫ ቦርድ የተገለፀው የክልሉ የምርጫ ውጤት፥ ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ውስጣዊና ውጫዊ ጫና ተቋቁማ ሉዐላዊነት ሀገር መሆኗን ለወዳጅም ለጠላትም ያስመሰከረችበት ነው ብሏል።
ምክርቤቱ አያይዞም ምርጫው በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል።
የምክርቤቱ ሰብሳቢ አቶ መሀመድ ሁሴን አደም ፥ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች በምርጫ መፎካከር ብቻ ሳይሆን በእያንዳንዱ የመንግስት ፖሊሲ ላይ ሲያደርጉት የነበረው የነቃ ተሳትፎ ለምርጫው ነፃና ፍትሃዊት አበርክቶ ነበረው ብለዋል።
የምርጫ ሂደቱ ከቅድመ እስከ ድህረ ምርጫ ድረስ ሰላማዊ እንደነበር የጠቆመው ምክርቤቱ፥ በክልሉ መንግስት ለመመስረት የሚያበቃውን ድምፅ ላገኘው የብልፅግና ፖርቲ መልካም ምኞቱን ገልጿል።
6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድም የበኩላቸውን ድርሻ ለተወጡት ሰባት የተፎካካሪ ፖርቲዎች ጨምሮ ለሃይማኖት አባቶች፣ለሀገር ሽማግሌዎችና ለፀጥታ አካላት ምክርቤቱ ምስጋናውን አቅርቧል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
54
Engagements
Boost Post
47
3 Comments
4 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.