Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል የኦሮሞን የስነ-ፅሁፍና ስነ-ጥበብ ከማሳደግ አንፃር በትኩረት ሊሰራ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የኦሮሞን ስነ-ጥበብና ስነፅሁፍ ማሳደግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ፓናል ውይይት አካሄደ፡፡

የክልሉ ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ ወይዘሮ አዲስአለም በዛብህ እደተናገሩት የኪነጥበብ ሙያ ለአንድ ማህበረሰብ እድገት ያለው ድርሻ ከፍተኛ ነው።

በተለይም ትውልድ ለመቅረጽ እንዲሁም ቋንቋ፣ ባህልና ታሪክን ለማሳደግ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

ኪነጥበብና እና የስነጥበብ ሙያ በክልሉ በሚፈለገው ደረጃ እድገት አላሳየም ያሉት አፈጉባኤዋ ሆኖም በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ኪነ ጥበብን ለማሳደግና ለማጎልበት የክልሉ ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ አበረታች ስራዎች እያከናወነ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡

የኦሮሞን ኪነጥብና ስነፅሁፍ ወደፊት ለማራመድ በመንግስት ጥረት ብቻ ውጤት ማስመዝገብ እንደማይቻል የገለፁት አፈጉባኤዋ በተለይም የባለድርሻ አካላት አስተዋፅኦ ወሳኝ በመሆኑ የሚመለከተው ሁሉ በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ መስራት እንዳለበት አንስተዋል፡፡

የክልሉ ባህልና ቅርስ ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሚልኬሳ አህመድ በበኩላቸው በአርቱና በኪነጥበብ ዘርፍ ማነቆ የሆኑትን በመለየት ለቀጣይ አቅጣጫና መፍትሄ ሀሳቦችን በማመንጨት ኪነጥበብና ስነፅሁፍ እንዲጎለብትና እንዲያድግ መድረኩ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡

በተለይም የኦሮሞን ኪነጥበብ በማሳደግ ረገድ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራራቸውን ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት ምክትል ቢሮ ሃላፊው የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡

የተጀመረው ሃገራዊ ለውጥ ከግብ እንዲደርስም የኪነ ጥበብ ዘርፍ የሚጠበቅበትን ሚና መጫወት ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል።

አያይዘውም በክልሉ ያሉትን የብሔር የብሔረሰቦች ኪነ ጥበብ በተቀናጀ መልኩ ለማሳደግ እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ ላይ በኦሮሞ ኪነጥበብና ስነፅሁፍ ዙሪያ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.