Fana: At a Speed of Life!

በሀረር ከተማ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና የከተማ ውበት ላይ ያለው ተሳትፎ መጎልበት አለበት ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሀረር ከተማ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ፥ አረንጓዴ ልማትና የከተማ ውበት ላይ ያለውን ተሳትፎ ማጎልበት እንደሚገባ ተገለጸ።

የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ በቀለ ተመስገን እንደገለጹት ሀረር ከተማን ወደቀድሞ ፅዱና ማራኪ ገጽታዋ ለመመለስና የተሻለች ከተማ ለማድረግ ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል።

የከተማውን ገጽታ ለመቀየር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በዚህም በስድስት ወራት ውስጥ ከ500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎችን የስራ እድል ለመፍጠር እንደተቻለ እና ከእነዚህ ውስጥም የጎዳና ተዳዳሪዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም የከተማዋን ጽዳት ለመጠበቅ ቤት ለቤት ቆሻሻ የመሰብሰብ ስራ መጀመሩ ተገልጿል።

በምስራቅ ኢትዮጵያ ደረጃ ቆሻሻን ወደ ምርት ለመቀየር እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ስራ አስኪያጁ ይህም በቀጣይ ለከተማው ፅዳት የላቀ አስተዋጾ እንዳለውም አመልክተዋል፡፡

ከቄራ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የእርድ ስርዓት ቁጥጥር የማሻሻያ ስራዎች መሰራቱን የሀረሪ መገናኛ ብዙሀን አስታውቋል።

የአረንጓዴ ልማት ችግኝ ተከላ፣ የመናፈሻ ቦታዎች ልማት እና ለአረንጓዴ ቦታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲኖራቸው የማድረግ ስራዎች በትኩረት እንደሚሰራ ተነግሯል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.