Fana: At a Speed of Life!

በሀሰተኛ ሰነድ ተጠቅሞ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ የነበረ ገጀራ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሀሰተኛ ሰነድ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ የነበረ ገጀራ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከ15 ቀን በፊት በአስመጪ ዳዊት የማነ ስም ብዛቱ 186 ሺህ 240 የሆነ ገጀራ በአራት ባለ 20 ጫማ ኮንቴነሮች ከቻይና ተጭኖ ሞጆ ጉምሩክ ተጓጉዞ ከደረሰ በኃላ እቃው በዲክላራሲዮን ቁጥር 4-1919/21 ተመዝግቦ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ የተፈቀደለት በማስመሰል እና ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ ለገቢ ዕቃ አወጣጥ የሰነድ መርማሪው አቅርቦ ሰነዱ ተመርምሮ ከ7 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ ከፍሎ እቃው ከተለቀቀ በኋላ ሃሰተኛ ሰነድና ዕቃውም ፍቃድ ያልተሰጠው ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ጉምሩክ ኮሚሽን እና በሞጆ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኢንተለጀንስ በኩል ክትትል ተደርጎ የቀረበው ሰነድ ሲጣራ ሐሰተኛ እና እቃውም ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ ፈቃድ ያልተሰጠው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ጉዳዩ ከ15 ቀን በፊት የተፈጸመ ቢሆንም፤ አስመጪው ያቀረብኩት ሰነድ ህጋዊ ነው በማለት ቅሬታ ስላቀረበ ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጋር በጋራ ሲጣራ ቆይቶ በተደረገው ማጣራት ሰነዱ ሐሰተኛ እና ከፌደራል ፖሊስ ፍቃድ ያልተሰጠው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በተጨማሪም በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኛ የእጅ ገጀራው ተገቢውን የጉምሩክ ስነ-ስርዓት በመፈጸም እንዲስተናገድ የሚገልጽ ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ለማውጣት የተሞከረ ሲሆን፤ ይህም ሐሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል ነው የተባለው፡፡

ይህን መነሻ በማድረግም በፌዴራል ፖሊስ ለሞጆ የወንጀል ምርመራ ማስተባባሪያ ፅህፈት ቤት መረጃውን በመስጠት በተደረገው ክትትል የእቃው ባለቤት እና ትራንዚተሩ ተይዘው ጉዳዩ በምርመራ ላይ ይገኛል፡፡

ገጀራ ክልከላ ከተደረገባቸው እቃዎች አንዱ ሲሆን፤ ከፌደራል ፖሊስ ሕጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ማስገባት የተከለከለ ነው፡፡

በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በጉምሩክ ኮሚሽን ባለሙያ እቃው እንዲወጣ የተፈቀደበት ደብዳቤ በማስመሰልና ሐሰተኛ የደብዳቤ ፎቶ በመጠቀም አስመጪው ሕጋዊ እንደሆነ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑንም ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.