Fana: At a Speed of Life!

በሀብሩ ወረዳ ከ3 ሺህ በላይ ጥይቶችና የምግብ ዘይት የተገኘባቸው ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ከ3 ሺህ በላይ የብሬንና የክላሽንኮቭ ጥይቶች እንዲሁም የምግብ ዘይት በህገ ወጥ መንገድ ሲያጓጉዙ የተገኙ ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።
የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አለልኝ በለጠ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ መሰረት ነው።
በዚህም የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-27129 አ.ማ የሆነ ተሽከርካሪ ከሃራ ከተማ ተጭኖ ወደ መርሳ ከተማ ሊገባ የነበረ 3 ሺህ 184 የብሬን ጥይትና 31 የክላሽንኮቭ ጥይት እንደያዘ ትናንት ሌሊት መያዙን ገልጸዋል።
አሽከርካሪውን ጨምሮ 5 ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም 190 ባለ 25 ሊትር ጀሪካን የምግብ ዘይት በህገ ወጥ መንገድ በተሽከርካሪ ጭነው ከሃራ መስመር ወደ መርሳ ሲያጓጉዙ የነበሩ አሽከርካሪውን ጨምሮ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡
አካባቢውን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ የሚሰሩ የግል ጥቅመኞች መኖራቸውን የተናገሩት ዋና ኢንስፔክተሩ÷ “ህብረተሰቡ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ተቀናጅቶ ሴራውን ማክሸፍ ይጠበቅበታል” ብለዋል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.