Fana: At a Speed of Life!

በሀዋሳ ባዕድ ነገር ጨምረው እንጀራ በመጋገር ሲያከፋፍሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባዕድ ነገር ጨምረው እንጀራ በመጋገር በህገወጥ መንገድ የሚያከፋፈሉ ተጠርጣሪዎች በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ።

ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በታቦር ክፍለ ከተማ ከወልደአማኑኤል ዱባለ አደባባይ አለፍ ብሎ በሚገኘው መንገድ 500 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ሙሉ ግቢ ተከራይተው ህገወጥ ተግባር ሲፈፅሙ የተገኙት ተጠርጣሪዎች ህብረተሰቡ ባደረገው ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ የገለፀው።

ፖሊስ ህገወጥ ተግባር በሚፈፅሙ አካላት ላይ አስፈላጊውን ማጣራት አድርጎ በህግ አግባብ ተጠያቂ የሚያደርግ መሆኑንም አስታውቋል።

ህብረተሰቡ መሰል ተግባር ሲያጋጥመው ጥቆማ የማድረግና አካባቢውን በንቃት የመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የከተማው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጥር አቅርቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.