Fana: At a Speed of Life!

እያንዳንዳቸው 64 ሲም ካርዶችን የሚይዙ ሁለት የቴሌኮም ማጭበርበሪያ መሳሪያዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ  በሀዋሳ ጉሙሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በኩል ወደ አዲስ አበባ ሊገቡ የነበሩ ሁለት የቴሌኮም ማጭበርበሪያ መሳሪያዎች መያዙን አስታወቀ፡፡

በኢመደኤ የቴክኖሎጂ ቁጥጥር ክፍል የእውቀት አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ አብርሃም ገ/መስቀል÷ በሀዋሳ የጉሙሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈትቤት ሁለት የቴሌኮም ማጭበርበሪያ መሳሪያዎች እያንዳንዳቸው 64 ሲም ካርዶችን የሚይዙ እና  ለዚሁ እኩይ ተግባር ማስፈጸሚያነት የሚውሉ የተለያዩ አጋዥ መሣሪያዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡

የቴሌኮም ማጭበርበርያ መሳሪያዎች ወደሀገር ውስጥ እንዲገቡ የሚደረጉት ብዙ ጊዜ በህገ-ወጥ መንገድ እንደሆነና ዓላማቸውም የራሳቸውን የኢኮኖሚ ትርፍ መሠረት አድርገው በሚሰሩ ግለሰቦች እና ድርጅቶች መሆኑን አቶ አብርሃም ጠቁመዋል፡፡

በኤጀንሲው የሴኩሪቲ ክሊራንስ ማዕከል የቁጥጥርና ክትትል ኃላፊ አቶ ሙህዲን ተማም  በበኩላቸው÷ የቴሌኮም ማጭበርበሪያ መሳሪያዎቹ ወደሀገር ውስጥ ገብተው ለመጡበት ዓላማ ውለው የነበረ ቢሆን በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሱ እንደነበረ አውስተው ኤጀንሲው በሰራው ስራ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 19 ሚሊየን ብር የሀገር ሀብትን ከኪሳራ መታደግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በኢመደኤ የሴኪሪቲ ክሊራንስ ማዕከል ከዚህ ቀደምም ለስለላ አገልግሎት የሚውሉ ካሜራዎች፣ ለተለያየ አሉታዊ ተልዕኮ መዋል የሚችሉ ከፍተኛ አቅም ያላቸው ኮምፒውተሮች፣ ድሮኖች ፣  የኮሙዩኒኬሽን እቃዎች እና ሌሎች በርካታ የቴሌኮም ማጭበርበሪያ መሳሪያዎች በህገወጥ መንገድ ወደሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ከጉሙሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ጋር በመተባበር የቁጥጥር ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.