Fana: At a Speed of Life!

በሀይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን የሚከናወነው የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የንቅናቄ መድረክ በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሀይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን የሚከናወነው የሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃማነት የንቅናቄ መድረክ በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ተካሂዷል።

በንቅናቄ መድረኩ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ የፌዴራል እና የደቡብ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ባደረጉት ንግግር በሀይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽ አማካይነት በሴቶና ህጻናት እንዲሁም በፖርኮችና በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ በተከናወኑ ተግባራት በርካታ ዜጎች ተጠቃማ ሆነዋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ኦውት ሆሎፔይን በበኩላቸዉ የሴቶችና ወጣቶችን አቅም ለማጎልበት በሚደረገው ጥረት ከፋውንዴሽኑ ጋር ኤምባሲው በትብብር እየሰራ ስለመሆኑ በመጥቀስ የሴቶችን ሁለንተናዊ አቅም ማጎልበት በቀጥታ የህብረተሰቡን አቅም ከፍ ማድረግ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

የሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ውዴታ ሳይሆን ሰብአዊ ግዴታ ነው ማለታቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.