Fana: At a Speed of Life!

በሀዲያ ዞን ከ16 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የፈሳሽ ናይትሮጅን ማምረቻ ፋብሪካ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል ሀዲያ ዞን ከ16 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የፈሳሽ ናይትሮጅን ማምረቻና የእንስሳት ዘር ማቆያ ፋብሪካ ስራ ጀመረ።

በመምሪያው የፈሳሽ ናይትሮጅን ባለሙያ አቶ ገዛኸኝ አሰፋ ፋብሪካው አየርን በመሰብሰብ የተቃጠለ አየር እና ውሃን ወደ ውጭ በማውጣት ከዜሮ በታች 96 በሆነ ቅዝቃዜ ናይትሮጅንን ለይቶ በማውጣትና በማጠራቀም ወደ ፈሳሽ በመቀየር በሰዓት 10 ሊትር ፈሳሽ ናይትሮጅን ያመርታል ብለዋል።

በተጨማሪም የተሻሻሉ የእንስሳት ዘርን በቅዝቃዜ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በማቆየት በተፈለገው ጊዜና ሰዓት ለመጠቀም እንደሚረዳም አብራርተዋል።

በደቡብ ክልል እንስሳትና አሳ ሀብት ቢሮ የግብዓት አቅርቦት እና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር መለሰ ጋሼ በበኩላቸው ፋብሪካው በክልሉ መንግስት ወጪ መገንባቱን ገልፀዋል።

የተሻሻለ የእንስሳት ዝርያ ፍላጎት በክልሉ እያደገ በመምጣቱ ፋብሪካው የአቅርቦት ክፍተቱን ለመቅረፍ እንደሚረዳም ተናግረዋል።

መረጃው የደቡብ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.