Fana: At a Speed of Life!

በሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረቂቅ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረቂቅ ላይ ውይይት ተካሄደ።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አዲስ ባዘጋጀው ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ረቂቅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
ዓለም አሁን ያለችበትን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ደረጃ የሚመጥን የሳይበር ምኅዳር መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቁ መዘጋጀቱ ተገልጿል።
በሌላ በኩል የሳይበር ምኅዳሩ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ያለበት በመሆኑ ሰነዱ ይህን መቋቋም የሚያስችል አሠራር መዘርጋትን ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል።
ከዚህ ባለፈም የሀገርን ደህንነት ማስጠበቅ እንዲሁም ሳይበርን በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ዘርፎች መጠቀም እንዲቻል የበይነ መረብ ደህንነትን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ ምኅዳሩን በጠንካራ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ መደገፍ እንደሚያስፈልግ መገለጹን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People Reached
13
Engagements
Boost Post
10
2 Comments
1 Share
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.