Fana: At a Speed of Life!

በሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን የተዘጋጀ የሙዚቃ ሽልማት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን የተዘጋጀ የሙዚቃ ሽልማት በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡

የሽልማቱ ዓላማ÷ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ዐሻራ ለማስቀጠል እና የኦሮሞን ኪነ ጥበብ ለማበረታታት መሆኑ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ በተደረገው የሙዚቃ ውድድር አሸነፊ ለሆኑ አርቲስቶች ሽልማት እና እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ለአርቲስት ሀሎ ዳዌ፣ ለአርቲስት ኢብራሂም አደም እና ለአርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል፡፡

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ባለቤት ወ/ሮ ፋንቱ ደምሱ፣ ሀጫሉ እድሜ ልኩን ለኦሮሞ ሕዝብ ሲታገል የኖረ አርቲስት እንደነበር ገልጸው፥ የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን አርቲስቱ የተሰዋለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ይሰራል ብለዋል፡፡

የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን የሙዚቃ ሽልማቱን በቀጣይ በአፍሪካ ደረጃ ለማዘጋጀት እንደሚሰራ ያስታወቁት ወ/ሮ ፋንቱ ፥ የሙዚቃ ሕልማቱ በየዓመቱ ይካሄዳል ብለዋል፡፡

የዘንድሮው ሽልማት የመጀመሪያው ሲሆን÷ ከዚህ በኋላ በየዓመቱ ሰኔ 22 ቀን እንደሚካሄድም ነው የተገለጸው፡፡

አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ካረፈበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም በአፋን ኦሮሞ የተሠሩ ሙዚቃዎች ለውድድር እንደሚቀርቡም ተመላክቷል፡፡

በኦብሴ ዋጋሪ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.