Fana: At a Speed of Life!

በሁርሶ፣ ጦላይና ብርሸለቆ የሰለጠኑ ምልምል ወታደሮች የምረቃ ስነስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁርሶ፣ ጦላይና ብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲሰለጥኑ የነበሩ ምልምል ወታደሮች የምረቃ ስነስርዓት ተካሄደ።

በዝግጅቱ ላይ የመከላከያ የሰላም ማስከበር ማዕከል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ደስታ አብቼን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ  አመራሮች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ተመራቂ ምልምል ወታደሮችም በክብር እንግዶቹ ፊት የተለያዩ  ወታደራዊ ትዕይንቶች አቅርበዋል።

ሰልጣኞቹ በፍላጎታቸው ወደ መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀልና መስፈርቱን በማሟላት በዛሬው ዕለት በየማሰልጠኛ ተቋሙ መመረቃቸውን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል።

ተመራቂ ምልምል ወታደሮቹ የአካል ብቃት፣ የተኩስና የስልት ስልጠናዎችን በመውሰድ ከፍተኛ አቅም መገንባታቸውን በተግባር እንዳሳዩ መገለፁን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ተመራቂ ምልምል ወታደሮች ሁርሶ፣ ጦላይና ብርሸለቆ በሚገኙ የወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ናቸው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.