Fana: At a Speed of Life!

በህንድ ለመጀመሪያ ጊዜ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ200 ሺህ ሰዎች በላይ ኮቪድ 19 ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ ለመጀመሪያ ጊዜ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከ200 ሺህ 739 ሰዎች በላይ ኮቪድ 19 እንደተገኘባቸው የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በአንድ ቀን በዚህ ቁጥር በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ሲገኙ በህንድ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት የሆስፒታል አልጋዎችና የኦክስጅን እጥረት ማጋጠሙንም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

እስካሁን በሀገሪቱ ከ14 ሚሊየን በላይ ህንዳውያን በወረርሽኙ ተይዘዋል፡፡

በ24 ሰዓታት ውስጥ1 ሺህ 38 ሰው ለህለፈት የተዳረገ ሲሆን የሟቾቹን ቁጥር ወደ 173 ሺህ 123 አድርሶታል፡፡

ከክትባት ጋር በተያያዘ ህንድ 111 ሚሊየን ዜጎቿን መከተቧን አስታውቃለች፡፡

ከነዚህ መካከልም 13 ሚሊየን የሚሆኑት ሁለተኛ ዙር ክትባት መውሰዳቸው ነው የተገለጸው፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.