Fana: At a Speed of Life!

በህንድ መንገድን ወደ መማሪያ ክፍል የቀየረዉ መምህር

አዲስ አበባ፣መስከረም 11፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰት ተከትሎ ተስተጓጉሎ የነበረዉን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል በመንግስት የሚተዳደሩ እና በገጠር አካባቢዎች ያሉ ትምህርት ቤቶች ተግዳሮት ገጥሟቸዋል።
ሆኖም የመማር ማስተማር ሂደት ለመቋቋምም በሕንድ ምዕራብ ቤንጋል ግዛት ውስጥ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ዲዊፕራናያን ናይክ ተማሪዎችን ጎዳና ላይ ሲያስተምር ተስተዉሏል።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት በሕንድ ትምህርት ቤቶች ከአንድ ዓመት በላይ ተዘግተዉ የነበረ ቢሆንም ተግዳሮቱን ወደ ዕድል ቀይሮ የሕንፃዎችን ግድግዳ እንደ ጥቁር ሰሌዳ በመጠቀም መምህሩ መንገድ ላይ እያስተማረ ይገኛል ነዉ የተባለዉ፡፡
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎች ወረርሽኙ ከተከሰተ ጀምሮ የመማሪያ ቁሳቁሶች እጥረት ይገጥማቸዉ እንደነበርና የመምህሩ አዲስ የማስተማር ዘዴ ይሄንን ችግር ሊፈታ እንደሚችል ቢቢሲ በዘገባዉ አስፍሯል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.