Fana: At a Speed of Life!

በህንድ በአንድ ቀን ብቻ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሰው በኮቪድ-19 ህይወቱ አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 30፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ በ24 ሰዓት ውስጥ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ሰዎች ህይወት በኮቪድ-19 ማለፉ ተነገረ፡፡

በህንድ በአንድ ቀን ብቻ የ904 ሰዎች ህይወት በኮሮናቫይረስ ሲያልፍ በአጠቃላይ በአገሪቱ በቫይረሱ የሞቱትን ሰዎች ቁጥር ወደ 40 ሺህ ከፍ ማለቱን የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በ24 ሰዓታት ውስጥ 56 ሺህ 282 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ይህም አጠቃላይ ቁጥሩን ወደ 2 ሚሊዮን አስጠግቶታል ነው የተባለው፡፡
አገሪቱ በአንድ ወር ውስጥ የ20 ሺህ ሰዎች ህይወት በፍጥነት እየተዛመተ ባለው ወረርሽኝ ምክንያት አልፏል ፡፡

ሆኖም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ባለፉት 14 ቀናት ውስጥ ከ63 ወደ 67 በመቶ ማደጉም መልካም ዜና ሆኖ እየተነገረ ነው፡፡

ወደ 600 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችም ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ነው መረጃው የሚያመለክተው ፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.