Fana: At a Speed of Life!

በህንድ የሚማሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከ250 ሺህ ብር በላይ ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ የሚማሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከ250 ሺህ ብር በላይ ለገሱ።

በሀገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ከ1 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎች ናቸው በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚውል የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉት።

በህንድ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶክተር ትዝታ ሙሉጌታ እንደገለጹት፥ ኤምባሲው በኢሜል፣ በፌስቡክ፣ በተማሪ አደረጃጀት እንዲሁም በምስል የተቀነባበረ ዘዴ በመጠቀም ለተማሪዎቹ ስለወረርሽኙ አስከፊነትና ጥንቃቄ እያስገነዘበ ነው።

የቫይረሱ ስርጭት በቁጥጥር ስር እስከሚውል ድረስም ይህ ስራ እንደሚቀጥል አምባሳደር ትዝታ ተናግረዋል።

ተማሪዎቹ ላደረጉት የገንዘብ ድጋፍ በኤምባሲው ስም አምባሳደሯ ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.