Fana: At a Speed of Life!

በህንድ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ዓለም አቀፍ ስጋት ነው – የዓለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት በሕንድ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ዝርያ በዓለም አቀፍ ስጋትነት ፈርጆታል፡፡

ድርጅቱ ቢ.1.617 የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ከሌሎች የቫይረሱ ዝርያዎች በላይ በቀላሉ የሚተላለፍ መሆኑን ባደረገው ጥናት ያመላከተ ሲሆን፥ ሌሎች ጥናቶች እየተደረጉ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ቫይረሱ እስካሁን በ30 ሃገራት መሰራጨቱንም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ከእንግሊዝ ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ብራዚል የታዩት ሌሎች የቫይረሱ አዲስ ዝርያዎች ተመሳሳይ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በህንድ በአሁኑ ወቅት ለበርካታ ሰዎች ህልፈት እና በየቀኑ በቫይረሱ ለሚያዙት በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ምክንያት ይህ የቫይረሱ ዝርያ መሆን አለመሆኑ ጥናት እየተደረገበት እንደሚገኝም ነው የተነገረው፡፡

በህንድ እስካሁን ከ22 ሚሊየን 900 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፥ ከ250 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ እና ዎርልድ ኦ ሜትር

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.