Fana: At a Speed of Life!

በህክምና እጥረት ህይወቱን የሚያጣ ተዋጊ ቁስለኛ እንዳይኖር እየሰራን ነው-ኮ/ል ኤፍሬም አመንቴ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወሎ ግንባር ወታደራዊ የህክምና ቡድን በህልውና ዘመቻው ላይ ተሰልፎ ለሰራዊቱ ውጤታማ አገልግሎት በመሰጠት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ።
በህክምና እጥረት ህይወቱን የሚያጣ ተዋጊ ቁስለኛ እንዳይኖር ሙሉ አቅማችንን ተጠቅመን እየሰራን መጥተናል ሲሉ የክፍለጦር ጤና ቡድን መሪ ኮሎኔል ኤፍሬም አመንቴ ገለጹ።
ኮሎኔል ኤፍሬም አመንቴ በቀጣይም ይህንኑ ተግባራችንን አጠናክረን እናስቀጥላለን ብለዋል።
በግንባሩ የዕዝ ጤና መምሪያ ሃላፊ ኮሎኔል ሙክታር ሁሴን ፥ የህክምና ቡድኑ ከአሸባሪው የህውሃት ወራሪ ጀሌ ጋር እየተካሄደ ባለው የህልውና ዘመቻ የመቁሰል አደጋ ለደረሰባቸውና ተጓዳኝ ህመም ለሚያጋጥማቸው የፀጥታ ሃይሉ አባላት ተገቢውን የህክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በሜካናይዝድ ክፍለጦር የጤና ቡድን መሪ ሻለቃ መንገሻ አስናቀ በበኩላቸው፥ በተያዘው የህልውና ዘመቻ የሃገራችን ሲቪል የህክምና ተቋማት ለሰራዊቱ እየሰጡ ያሉት አገልግሎት ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል።
በግንባሩ የዕዝ ችፍ ክሊኒካል ኦፊሰር ሻለቃ አገኘሁ መንግስቴ ፥በበጎ ፍቃደኝነት አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ሲቪል የህክምና ሙያተኞችን ማመስገናቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.