Fana: At a Speed of Life!

በህወሓት ውስጥ ያለው ቡድን በርካታ ነዋሪዎችን አፍኖ በመውሰድ ሰውሯቸዋል- የዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህወሓት ውስጥ ያለው ቡድን በርካታ ነዋሪዎችን አፍኖ በመውሰድ እንደሰወራቸውና እስካሁንም ያሉበት እንደማይታወቅ የዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

የዳንሻ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ከጽንፈኛው የህወሓት ቡድን ነፃ መውጣቷን አስመልክቶ ደስታቸውን ገልፀዋል።

የከተማዋ ጤና ተቋማት፣ ሱቆች፣ ሆቴሎች፣ የትራንስፖርትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተከፍተው ነዋሪዎች ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ገብተዋል።

ነዋሪዎቹ የህወሓት ፅንፈኛ ቡድን በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ የክህደት ጥቃት ከማድረሱ በፊት ከፍተኛ ሰብዓዊ ጉዳት ይደርስባቸው እንደነበርም ይናገራሉ።

በሰርግና በለቅሶ ላይ በአለባበሳቸው ጭምር በህወሓት ካድሬዎችና የፀጥታ ኃይሎች ይጠየቁ እንደነበር በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

ዜጎች መብታቸውን ሲጠይቁ የሚታሰሩበት፣ የሚገረፉበት እንዲሁም የሚገደሉበት ሁኔታ እንደነበርም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

ቡድኑ እስካሁን ለውጥና ሰላም እንዳይመጣ ሲሰራ እንደነበርም ነዋሪዎቹ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በአሁኑ ወቅት መንግሥት በጽንፈኛው የህወሓት ታጣቂ ኃይል ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደግፋለንም ነው ያሉት፡፡

በቀጣይ መከላከያ ሰራዊቱን ለማጠናከር ድጋፍ እናደርጋለንም ብለዋል።

መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጽንፈኛው ቡድን እስከሚደመሰስ ድረስ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እንዲደግፍ ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.