Fana: At a Speed of Life!

በህወሓት ጁንታ ላይ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ የሀገር ሉዓላዊነትን እና የህግ የበላይነትን የማስከበር ተልዕኮ ነው- የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህወሓት ጁንታ ላይ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ የሀገር ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን የማስከበር ተልዕኮ ያለው መሆኑን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ፡፡

የኦሮሞ ህዝብ ለሀገር ግንባታ የማይተካ ሚና ሲያበረክት መቆየቱን እና እያበረከተ እንዳለ የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡

አሁን እንደ ሀገር ተገደን የገባንበት ዘመቻም ሀገር የማስቀጠልና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ እንደሆነ ጠቅሷል፡፡

ህዝባችን ከሌሎች የሀገሪቷ ዜጎች ጋር በጋራ በመሆን ኢትዮጵያ ላይ ከውጭ የሚቃጣባትን ወረራ በመመከት ጉልህ ድርሻ አበርክቷል፤ አሁንም እያበረከተም ይገኛል ነው ያለው የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ባወጣው መግለጫ፡፡

አሁንም የህግ የበላይነትን ለማስከበርና የሀገር አንድነትን ለማረጋገጥ ከመቸውም ግዜ በላይ እየሰራ ይገኛል ብሏል፡፡

ከውጭም ይሁን ከውስጥ ሀገር ለማተራመስና ለማፍረስ የሚሸረቡ ሴራዎችን በማክሸፍ እና የኢትዮጵያን ሉኣላዊነትና አንድነት ለማረጋገጥ ከብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር ደምና አጥንቱን ገብሯል ብሏል ቢሮው፡፡

ዴሞክራሲ እንዳይጎለብት፣ የሀገር አንድነት እንዳይፀና፣ የህዝቦች በጋራ የመኖር፣ የመንቀሳቀስና ሀብት የማፍራት መብት እንዳይረጋገጥ የሚሰሩ ኃይሎችን በማስወገድ ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር እንድትሆን የኦሮሚያ ክልል መንግስትና ህዝብ ከሌሎች የሀገሪቱ ህዝቦች ጋር በጋራ እንደሚሰራ ለማሳወቅ ይወዳልም ብሏል፡፡

በህወሓት የጥፋት ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ እስኪጠናቀቅ ሁለንተናዊ ድጋፍና ርብርብ እንደሚያደርግም አሳውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ለየትኛውም ሀገር አፍራሽ ጽንፍ ሳይበገር ለሚወዳት ሀገሩ በጋራ እንዲቆምም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከህግና ህገመንግስታዊ ስርዓት ያፈነገጠውን የህወሓት ጁንታ ቡድን በማንበርከክ የህግ የበላይነትን፣ ሀገራዊ አንድነትንና ሉኣላዊነታችንን በህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንትጋ ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡

በህግና ህገመንግስታዊ አሰራር ፅንፈኞችን በማጋለጥ የሀገር አንድነትና ሉአላዊነት ይጠናከራልም ብሏል የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ በመግለጫው፡፡

የክልሉ ህዝብ ለኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ባደረገው ድጋፍና የህወሓት የጥፋ ቡድንን ለማውገዝ በተደረጉ ሰልፎች አጋርነቱን አሳይቷል ሲል አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.