Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከ 5 ሺህ 100 በላይ ተተኳሽ ጥይት ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከ5 ሺህ 100 በላይ ተተኳሽ ጥይት በማኅበረሰብ ጥቆማ መያዙን የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር እና የአርጎባ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ፅሕፈት ቤት አስታውቀዋል፡፡

የአርጎባ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ፅሕፈት ቤት ምክትል ኮማንደር መሐመድ ባህሪታ እንደገለፁት ÷ ከህዝብ በደረሰ ጥቆማ በወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት በተካሄደ ክትትል 1 ሺህ 900 “ኢንፎርት” ተተኳሽ ጥይቶች እና 60 የክላሽ ጥይቶች በድምሩ 1 ሺህ 960 ተተኳሽ ጥይቶች ተይዘዋል።

ጥይቶቹን የጫነው ባጃጅ ኬላ ጥሶ ከፀጥታ አካላት ለማምለጥ ሙከራ አድርጎ ነበር ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ጋዝጊብላ ወረዳ አንድ ግለሰብ ”ላልኪው” አካባቢ የሚገኘውን ኬላ በሌላ መንገድ በማሳበር በህገ ወጥ መንገድ 2 ሺህ 141 የክላሽ ጥይት በኬሻ ጠቅልሎ ወደ ላስታ ሊያሻግር ሲሞክር በወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በህግ ቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡

ኅብረተሰቡ የህገ ወጥ መሳሪያ ዝውውርንና ንግድን ለመከላከል በሚደረገው እንቅስቃሴ እያደረገ ያለውን ያልተቆጠበ ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ መተላለፉን ከኢዜአ እና ከአርጎባ ልዩ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.