Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ ወረራ የተያዘ 560 ሺህ 233 ካሬ መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲመለስ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በህገወጥ ወረራ የተያዘ 560 ሺህ 233 ካሬ መሬት በፍርድ ቤት እግድ ምክንያት ወደ መሬት ባንክ እንዲመለስ መወሰኑ ተገለጸ።
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣው መግለጫ÷በመዲናዋ በሚገኙ 10 ክፍለ ከተሞች በተደረገ የመሬት ዳሰሳ ጥናት፥ 560 ሺህ 233 ካሬ በህገወጥ ወረራ የተያዙ መሬቶች የፍርድ ቤት እግድ ምክንያት ወደ መሬት ባንክ እንዲመለሱ መወሰኑን አስታውቋል።
 
በኦዲት ግኝቱ ፍርድ ቤት እግድ የጣለባቸው ምንም አይነት የልማት ተግባር ያልተከናወነባቸው ባዶ መሬቶችን ጭምር መሆኑ ተመላክቷል፡፡
እግድ የተሰጣቸው ሰዎችም ምንም አይነት የባለመብትነት መረጃም ሆነ ማስረጃ የሌላቸው መሆኑን ከኦዲት ሪፖርቱ ማረጋገጥ መቻሉ ነው የተገለጸው።
 
ሕግና ስርዓት የማስከበር ስራ ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ መተግበር አለበት ብሎ የከተማ አስተዳደሩ በጽኑ እንደሚያምን በመግለጫው ተጠቁሟል።
 
ስለሆነም ጉዳዮ የሚመለከታቸው አካላት ህግና ስርዓትን ተከትለው ሃላፊነት በተሞላው ሂደት ሊሰሩ እንደሚገባ ጥሪ መቅረቡን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.