Fana: At a Speed of Life!

በሕገ ወጥ የነዳጅ ጥቁር ገበያ ምክንያት በማደያዎች አገልግሎት እያገኘን አይደለም – የአሶሳ ከተማ አሽከርካሪዎች

በሕገ ወጥ የነዳጅ ጥቁር ገበያ ምክንያት በማደያዎች አገልግሎት እያገኘን አይደለም – የአሶሳ ከተማ አሽከርካሪዎች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገወጥ የነዳጅ ጥቁር ገበያ ምክንያት ማደያዎች ላይ አገልግሎት እያገኙ አለመሆኑን በአሶሳ ከተማ የሚኖሩ አሽከርካሪዎች ተናገሩ፡፡
በከተማዋ 8 የሚደርሱ ማደያዎች ቢኖሩም ነዳጅ በተገቢው ሁኔታ እየቀረበ አለመሆኑን የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎቹ፥ 1 ሊትር ቤንዚን እስከ 200 ብር ለመግዛት መገደዳቸውን ተናግረዋል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በነበረው ቆይታ፥ ቤንዚን በፕላስቲክ ኮዳዎች እንደሚቸረቸር እና ሽያጩም ከመደበኛው ተመን እስከ 4 እጥፍ የሚደርስ መሆኑን ተመልክቷል፡፡
ስለችግሩ ከተጠየቁ የማደያ ባለቤቶች በአሶሳ ከተማ የተባበሩት ማደያ ስራ አስኪያጂ አህመድ ያሲን፥ መንገድ ላይ በሚገጥም የፀጥታ ችግር ምክንያት ነዳጅ ለማጓጓዝ አስቸጋሪ ሁኔታ በመፈጠሩ ከሁለት ወራት ወዲህ አቅርቦት እንደሌለ ተናግረዋል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሀሰን፥ የነዳጅ አቅርቦት ፈታኝ ሁኔታ መፍጠሩን አንስተዋል፡፡
የሰላም ችግር ነዳጅ ለማጓጓዝ አስቸጋሪ ሁኔታ መፍጠሩ፣ ክልሉ ከጂቡቲ ያለው ርቀት፣ ስግብግብ ነጋዴዎች የጥቁር ገበያ ንግድን ማስፋፋታቸው እክል መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡
መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሆኑን ጠቅሰው፥ በቅርቡ በተደረገ ክትትል 62 በርሜል ነዳጅ መያዙን ለአብነት አንስተዋል፡፡
ህግን የማስከበርና ሁኔታውን የማስተካከል እርምጃም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ከጎረቤት ሀገር ሱዳን ነዳጅ ለማስገባት የሚቻልበት ሁኔታ እየታሰበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.