Fana: At a Speed of Life!

በህጋዊ ንግድ ሽፋን ሊጭበረበር የነበረ ከ4 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህጋዊ ንግድ ሽፋን ሊጭበረበር የነበረ ከ4 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

የንግድ ማጭበርበሮቹ በቦሌ፣ አዳማ፣ ቃሊቲ እና ድሬዳዋ በሚገኙ የጉምሩክ ቅርንጫፎች ተደርሶባቸው የተሰበሰቡ መሆናቸው ታውቋል።

በዚህም ከነሐሴ 21 እስከ 28/2012 ዓ.ም ድረስ ብቻም ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎች ላይ ዋጋ አንሶ በማቅረብ፣ በተሳሳተ የታሪፍ አመዳደብ፣ በዝቅተኛ የስጋት ደረጃ የእቃ መልቀቂያ ተሰጥቶ በድንገተኛ ፍተሻ በተገኘ ልዩነት እና በሌሎች የንግድ ማጭበርበሮች ምክንያት መንግስት ሊያጣው የነበረ በድምሩ 4 ሚሊየን 408 ሺህ545 ብር እንዲከፍል ተደርጓል ነው የተባለው።

በትክክለኛ ታሪፍ ባለመመደባቸው ቀረጥና ታክስ ሊጭበርበርባቸው ከነበሩ ዕቃዎችም የሞባይል የጆሮ ማዳመጫ፣ የሞባይል ቻርጀር፣ አልባሳት፣ የኮምፒውተር መለዋወጫ እና የማምረቻ ግብዓቶች እንደሚገኙበት ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ይህም የተቋሙ ሰራተኞች ከግል ጥቅም ይልቅ ለሀገር መወገንናቸው እና መልካም ስነ-ምግባር ተላብሰው ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑ አንዱ ማሳያ ተብሏል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.