Fana: At a Speed of Life!

በህግ ቁጥጥር ስር በዋሉ 4 ሺህ 183 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሰረተ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በህግ ቁጥጥር ስር በዋሉ 4 ሺህ 183 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቁ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሁሴን ዑስማን እና በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል የወንጀል መርማሪ ኮሚሽነር ግርማ ገላን በጋራ በሰጡት መግለጫ የአርቲስቱን ግድያ ተከትሎ በተፈጠረ ግርግር የ167 ሰዎች ህይወት ሲጠፋ በ360 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ከ4 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙንም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ የ9 ሺህ 63 ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ በ559 የክስ መዝገቦች በማደራጀት 4 ሺህ 183 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱንም አስታውቀዋል፡፡

መረጃ ከተጣራባቸው መካከል 2 ሺህ 351 ተጠርጣሪዎች በክልል፣ 3 ሺህ 314 በፌደራል እንዲሁም 63ቱ ደግሞ በሀረሪ ክልል ክስ ተመስርቶባቸዋል ነው የተባለው፡፡

ከዚህ ባለፈ ግን 4 ሺህ 892 ምክር ተሰጥቷቸው ወደማህበረሰቡ የሚቀላቀሉ ይሆናል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.