Fana: At a Speed of Life!

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ለዘማች ቤተሰቦች የበዓል ስጦታ አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ለዘማች ቤተሰቦች እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ450 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የገና በዓል የፍጆታ እቃዎችን አበርክቷል፡፡
 
በዚህ መሰረትም ለአገር ህልውና በግንባር ህይወታቸውን መስዋዕት አድርገው እየተፋለሙ ለሚገኙ 25 የዘማች ቤተሰቦች እና ዘማቾች ለእያንዳንዳቸው 1 በግ፣ 25 ኪሎ የጤፍ ዱቄት፣ 3 ሊትር ዘይትእና 1ሺህ ብር ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
 
ከዚህ ባለፈም ወረዳው 315 ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ለእያንዳንዳቸው 1 ዶሮ ፣10 እንቁላል፣ 5 ኪሎ ሽንኩርት እና ዘይት አበርክቷል፡፡
 
ድጋፉ የተለያዩ አካላትን በማስተባበር የተበረከተ ሲሆን÷ለዚህም ወረዳው ምስጋና አቅርቧል፡፡
 
ሃይማኖት ኢያሱ እና ሂርጶ ሽቦ
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.