Fana: At a Speed of Life!

በሊበን ጃዊ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሸዋ ዞን ሊበን ጃዊ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
በአደጋው ሕይወታቸው ካለፉት በተጨማሪ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
የሊበን ጃዊ የትራፊክ አስተባባሪ ሳጅን ግዛቸው ዳማ እንደገለፁት ÷አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ነቀምት ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከነቀምት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበረ ሎንግ ቤዝ መኪና ጋር በመጋጨቱ የደረሰ ነው፡፡
በደረሰው አዳጋም ከአንድ ቤተሰብ እናትና ልጅን ጨምሮየሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ከምራብ ሸዋ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.