Fana: At a Speed of Life!

በላይና ተስፋ የመኪና መሸጫና ጓደኞቹ ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለጸጥታ ሃይሉ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በላይና ተስፋ የመኪና መሸጫና ጓደኞቹ ለመከላከያ ሰራዊት ለአማራ ልዩ ሀይል እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍን አደረጉ።

ወገኖቻችን ቤታችሁ ገብታችሁ እስክትቋቋሙ ድረስ አብረናችሁ ነን ያሉት አቶ በላይነህ ደበበ÷ የድርጅቱ ባለቤት ስለደረሰባችሁ ጉዳት በእጅጉ አዝነናል በማለት ተፈናቃዮችን አረጋግተዋል።

ኢትዮጵያዊነት በችግር ተፈትኖ ነጥሮ የሚወጣ ልዩ ክብር ነው፤ እኛም በዚህ ወቅት ከጎናችሁ መሆን ግዴታችን ነው፤ አሁንም ነገም አብረናችሁ ነን ብለዋል።

በላይና ተስፋ የመኪና መሸጫ እና ጓደኞቹ ወርጌሳ ከተማ በመገኘት 300 ኩንታል ዱቄት ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አድርገዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሁላችን በሰላም የመኖር ጋሻችን ነው ያሉት አቶ በላይነህ÷ ሰራዊቱን መደገፍ ሀገርን በጥብቅ ካስማነት እንደመገንባት ነው ብለዋል።

ለመከላከያ ሰራዊትና ለአማራ ልዩ ሀይል አባላት 30 ሠንጋ አስረክበዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ወልደ ተንሳኤ ስለተደረገላቸው ድጋ አመስግነዉ÷ የደረሰው ጉዳት አስከፊ ቢሆንም ኢትዮጵያዊነትን በኢትዮጵያውያን ላይ እንዲሰፍን አድርጓል ብለዋል።

በአለባቸው አባተ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.