Fana: At a Speed of Life!

በላ ሊጋው ሪያል ማድሪድ ሲያሸንፍ አትሌቲኮ አቻ ተለያይቷል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ላ ሊጋ ትናንት ሶስት ጨዋታዎች ተካሄደዋል።

የዋንጫ ተፎካካሪው ሪያል ማድሪድ ኤባርን አስተናግዶ ድል ቀንቶታል።

ማድሪድ በቶኒ ክሩስ፣ ሰርጂዮ ራሞስ እና ማርሴሎ ጎሎች ጨዋታውን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ቢጋስ የኤባርን ማስተዛዘኛ ጎል ማስቆጠር ችሏል።

በሌላ ጨዋታ ወደ ሳን ማሜስ ያቀናው አትሌቲኮ ማድሪድ ከአትሌቲክ ቢልባኦ ጋር አንድ አቻ ተለያይቷል።

ቢልባኦ በኢከር ሙናይን ጎል ቀዳሚ ቢሆንም በዲያጎ ኮስታ ጎል አትሌቲኮ ማድሪድ አቻ መሆን ችሏል።

በሜዳው ኦሳሱናን ያስተናገደው ሪያል ሶሲዬዳድም በተመሳሳይ ጨዋታውን አንድ አቻ ጨርሷል።

ሚኬል ኦያርዛባል ለሶሲዬዳድ አድሪያን ሎፔዝ ደግሞ ለኦሳሱና ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ከትናንት በስቲያ በተደረገ ጨዋታ ባርሴሎና ማሸነፉ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.