Fana: At a Speed of Life!

በላ ሊጋው ግራናዳ ሲያሸንፍ በኮፓ ኢታሊያ ጁቬንቱስ ለፍጻሜ አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ላ ሊጋ ትናንት ምሽት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

በሜዳው ጌታፌን ያስተናገደው ግራናዳ ዳኮናም እና ፈርናንዴዝ ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል።

ቲሞር ለጌታፌ የማስተዛዘኛ ጎሏን አስቆጥሯል።

በሌላ ጨዋታ ቫሌንሲያ በሜዳው ሌቫንቴን አስተናግዶ ሳይሸናነፉ አንድ አቻ ጨርሰዋል።

ከትናንት በስቲያ በተደረገ ጨዋታ ሲቪያ ሪያል ቤቲስን 2 ለ 0 ማሸነፉ አይዘነጋም።

ሌሎች ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ የሚካሄዱ ይሆናል።

በሌላ በኩል ትናንት ምሽት የኮፓ ኢታሊያ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ተካሄዷል።

ጁቬንቱስን ከኤሲ ሚላን ያገናኘው ጨዋታ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

በመጀመሪያው ጨዋታ ሳንሲሮ ላይ አንድ አቻ የተለያዩ ሲሆን፥ ጁቬንቱስ ከሜዳው ውጭ ባገባው ጎል ተጠቅሞ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።

በጨዋታው ክርስቲያኖ ሮናልዶ የፍጹም ቅጣት ምት ሲያባክን፥ የኤሲ ሚላኑ አጥቂ አንቴ ሬቢች በ16ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

ጁቬንቱስ ውድድሩን 13 ጊዜ በማሸነፍ ባለ ክብረ ወሰን ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.