Fana: At a Speed of Life!

በሌተናል ጄኔራል አበባው ታደሰና በሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ስም የተከፈተ ምንም አይነት የማህበራዊ ትስስር ገጽ እንደሌለ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሌተናል ጄኔራል አበባው ታደሰና ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ በስማቸው የከፈቱት ምንም አይነት የማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጽ እንደሌለ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ በሌተናል ጀኔራል አበባው ታደሰ እና በሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ስም ሀሰተኛ የፌስቡክ ገጽ ተከፍቶ የተዛባ መልዕክት እየተላለፈ እንደሚገኝ ገልጿል።
እነዚህ ሁለት ከፍተኛ ጀኔራል መኮንኖች ምንም አይነት ማህበራዊ ገጽ በስማቸው ያልከፈቱ መሆኑን እያረጋገጥን ፣ ህብረተሰቡ እንዳይደናገር እናሳስባለን ሲል አስታውቋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.