Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ለ119 አቅመ ደካማ ወገኖች የምግብ አቅርቦት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ ሀማሬሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለሚገኙ 119 አቅመ ደካማ ወገኖች የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ የምግብ አቅርቦት ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ድጋፉን የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር ያበረከተ ሲሆን÷ በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ÷ ክልሉ ያደረገው ድጋፍ በተለይም በረመዳን ፆም ወቅት አጋርነቱን ለመግለፅ ነው ብለዋል፡፡

ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰው÷ ዜጎቹ በዘላቂነት ራሳቸውን እንዲችሉ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት፡፡

በተለይም በረመዳን ወቅት እርስ በእርስ መረዳዳት አስፈልጊ መሆኑን አመላክተው÷ ህብረተሰቡም አቅመ ደካማ ዜጎችን ከመደገፍ አንፃር የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኢስማኤል ዩሱፍ ማዘጋጃ ቤቱ ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ለ119 አቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው÷ ለእያንዳንዱ ሰው 25 ኪሎ ግራም ፍርኖ ዱቄት እና 5 ሊትር የምግብ ዘይት እንዲደርስ ስለመደረጉ መናገራቸውን ከሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም በተለይም በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ የሚገኘውን የኑሮ ውድነት ችግር እንደሚያቃልል ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.