Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል የመንግስት ሰራተኞች የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወመውን ንቅናቄ ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል የመንግስት ሰራተኞች የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወመውን ንቅናቄ ተቀላቀሉ፡፡
በመርሃ ግብሩ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ፣ የብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብዱልጀባር መሃመድን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጣ ማንኛውንም የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደሚቃወሙ የንቅናቄው ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
የአሜሪካና አጋሮቿ እንቅስቃሴ አሸባሪዎችን ወደ ስልጣን መመለስ መሆኑን የተናገሩት ተሳታፊዎቹ ÷ ይህም በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ይከስማል ነው ያሉት።
ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ሳይረዱ ከአንድ ወገን የሆነ ውግንና ማሳየታቸው አገራቱ ለፍትህና ርትዕ ግድ የማይሰጣቸው መሆናቸውን አመላካች መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ህብረት በመፍጠር ይህንን እኩይ አላማ ማክሸፍ እንደሚጠበቅት ጥሪ አቅርበዋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.