Fana: At a Speed of Life!

በሐረር 10 ሺዎች የተሳተፋትበት የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረር ከተማ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የእስልምና ተከታዮች እና የሌሎች እምነቶች አባቶች የተገኙበት የጎዳ ላይ ኢፍጣር ተካሄደ ።
በኢፍጣር ስነስርዓቱ ላይ የተገኙ የእስልምና እምነት አባቶች “ቅዱሱን የረመዳን ወር ስንፆም ሚስኪኖችን በማሰብ በመርዳት መሆን አለበት” ብለዋል።

የረመዳን ወርን በመተጋገዝና በመረዳዳት እያሳለፉ እንደሚገኙ የገለፁት ምእመናን በበኩላቸው፥ ቀሪውን የፆም ጊዜ ይህኑን የመተሳሰብ እሴት ሀይማኖቱ በሚፈቅደው ሁሉ አጠናክረው ለመቀጠል ገብተዋል።

የኢፍጣር መርሃ ግብሩ በከተማው ከሚገኘው ራስ ሆቴል እስከ እስከ ሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ድረስ ነው የተካሄደው።

 

 

በእዮናዳብ አንዱዓለም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.