Fana: At a Speed of Life!

በሕዳሴ ግድብ ዙርያ ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መከላከያ የጦር ኃይል አመራሮች ገለጻ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙርያ ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ. መከላከያ የጦር ኃይል አመራሮች ገለጻ ተደርጓል።

በመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ የስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው መድረክ ላይ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙርያ ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ የጦር ኃይል አመራሮች ገለጻ አድርገዋል።

በገለጻ መርሐ ግብሩም ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አደም መሃመድ፣ ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ እንዲሁም በውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ መአረግ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ ተገኝተዋል።

የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ባደረጉት ገለፃም፥ በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መካከል ሲደረጉ የነበሩ የድርድር ሂደቶችን፣ የሕዳሴው ግድብን ግንባታ ሂደት፣ የአሞላልና አስተዳደር እቅድ፣ እንዲሁም የግንባታውን ሂደትና ያለበትን ደረጃ አንስተዋል።

በአሜሪካ እና በዓለም ባንክ ታዛቢነት የተደረጉ ውይይቶች ለምን ስኬታማ መሆን እንዳልቻሉም ለአመራሮቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ በየትኛውም ሀገር ላይ ተጽዕኖ እንደማያደርስ የጠቆሙት ሚኒስትሩ፥ ይልቁንም ለሱዳንም ይሁን ለግብፅ ጠቀሜታ እንዳለው መናገራቸውን ከውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.