Fana: At a Speed of Life!

በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የውጭ ሀገር ገንዘብ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሕብረተሰቡና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረን የውጭ ሀገር ገንዘብ መያዙን ገለፀ፡፡

በተካሄደው ዘመቻ 27 ሺህ 491 የአሜሪካ ዶላር፣ 15 ሺህ 325 ዩሮ፣ 680 ፓውንድ፣ 6 ሺህ 689 የኤርትራ ናቅፋ፣ 5 ሺህ 200 የስዊዝ ፍራንክ፣ 500 የአንጎላ ክዋንዛ፣ 1 ሺህ 680 የኳታር ሪያል፣ 1 ሺህ የኖርዌይ ክሮን እና 49 ሺህ 735 የኢትዮጵያ ብር እንዲሁም በርካታ የባንክ ደብተሮች ከ71 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያመጣው አደጋ ከባድ መሆኑን ተገንዝቦ ሕብረተሰቡ የሚያጠራጥሩ ነገሮችን ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኝ የፀጥታ አካላት በማሳወቅ የተለመደ ቀና ትብብሩን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት  ፖሊስ ጥሪ ማቅረቡን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.