Fana: At a Speed of Life!

በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ ከ84 ሺህ በላይ የተለያዩ ሃገራት ገንዘብ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር ሊወጣ የነበረን 84 ሺህ 587 የተለያዩ ሃገራት ገንዘብ መያዙን አስታወቀ።

በደወሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ 17 ሺህ 965 የአሜሪካ ዶላር፣ 2 ሺህ 520 ፖውንድ እና 64 ሺህ 102 የየመን ሪያል በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙንም አስታውቋል።

ሕገ ወጥ ገንዘቡ ወደ ብሔራዊ ባንክ ገቢ የተደረገ ሲሆን፥ አራት ተጠርጣሪ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።

ህብረተሰቡ መሰል ህገ ወጥ ተግባራትን ሲመለከት ጥቆማ በመስጠትና ተገቢውን ትብብር በማድረግ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ መቅረቡን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.