Fana: At a Speed of Life!

በመቀሌ ከተማ ድገፍ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ  ነው- አቶ አታኽልቲ ሃይለስላሴ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  በትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ በመቀሌ ከተማ ድገፍ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ እየተደረገ መሆኑን  የመቀሌ ከተማ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ ሃይለስላሴ ገለጹ።

በትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የመቀሌ ከተማ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ ሃይለስላሴ ÷ በከተማዋ ለሚኖሩና ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ለመጡ 379 ሺህ አቅመ ደካሞችና አረጋዊያን ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል  ዝግጅት ተጠናቆ እርዳታ እየቀረበ  ይገኛል ብለዋል።

እስካሁንም  ለ180 ሺህ ዜጎች ስንዴ እና ዱቄት እንዲሁም ለህጻናት ደግሞ አልሚ ምግቦች  መሰጠታቸውን ከንቲባው ገልጸዋል።

የተቀሩት ድጋፍ የሚሹ ወገኖች ደግሞ በቀጣይ ቀናት ውስጥ እርዳታው እንደሚሰጣቸው  አቶ አታኽልቲ   መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.