Fana: At a Speed of Life!

በመቀበር ላይ የሚገኘውን አሸባሪው ህወሓትን ለመታደግ የተካሄደው ምሥጢራዊ ስብሰባ ተጋለጠ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓትን ከሚቀበርበት ጉድጓድ ለመታደግ የሽብር ቡድኑ አባላትና ምዕራባውያን የጥቅም አጋሮቹ ዲፕሎማቶች ያካሄዱት ምሥጢራዊ ስብሰባ ተጋልጧል።
 
ብርሃነ ገብረ ክርስቶስና ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅን ጨምሮ የአሸባሪዎቹ ህወሃትና ሸኔ የውጭ አመራሮች፤ እንዲሁም የጥቅም አጋሮቻቸው ምዕራባውያንና ዳያስፖራዎች ወደ መቃብራቸው እየተሸኙ ያሉትን የሽብር ቡድኖች ለማዳን ድብቅ ምክክር አካሂደዋል።
 
ከዚህ በተጨማሪ በሶማሊያ የአሜሪካ አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ እና የቀድሞ የአሜሪካ የመከላከያ የአፍራካ ጉዳዮች ምክትል ሀላፊ ቪኪ ኹደልስተን፣ የአውሮፓና የእንግሊዝ ዲፕሎማቶች ወደ መቃብራቸው እየተሸኙ ያሉትን የሽብር ቡድኖች ለማዳን በስብሰባው ከተሳተፉት መካከል ናቸው።
 
በዚህ ምሥጢራዊ ስብሰባ “በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግስትን ልናስቆመው አንችልም የአፍሪካ ህብረት የወከላቸው የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትም ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ እኛ እንደምንፈልገው አልተንቀሳቀሱም” ማለታቸው ታውቋል።
 
እንደምንም ብለን አሁን በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት በማውረድ የምንፈልገውን የሽግግር መንግስት ማቋቋም ይኖርብናልም ሲሉም ነው የዶለቱት፡፡
 
በድርድርም ሆነ በየትኛውም ሁኔታ የአሸባሪውን ህወሓትና የጥቅም አጋሮቹን ፍላጎት የሚያስፈጽም መንግስት መቋቋም እንዳለበት የተነሳ ሲሆን ይህንንም ለማሳካት የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶችን ጨምሮ ሌሎች አካላትን መጠቀም ይጠበቅበናል ሲሉ ከንቱ ዕቅዳቸውን አቅርበዋል።
 
በሌላ በኩል አሸባሪውን ቡድን ወደ ስልጣን ለመመለስ እንደ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ያሉ ታዋቂ ግለሰቦች አሸባሪውን የሚደግፉ የአሜሪካ ባለስልጣናትን የማግባባት ሥራ ከመጋረጃ ጀርባ እያከናወኑ መሆኑም በዚህ ምሥጢራዊ ስብሰባ መዳሰሱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
አሸባሪውን ቡድን ወደ አዲስ አበባ ለማስገባት በዲፕሎማሲው መስክ ጫና ለማሳደር መንቀሳቀስ እንደሚገባም በሚስጢር መዶለታቸው ተረጋግጧል፡፡
 
በዋሺንግተን ዲሲ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተሳተፉት ግለሰቦች ዘጠኝ ሲሆኑ÷
 
1. ፕ/ር ኤፍሬም ይስሀቅ
2. ዶ/ር ኢሌኒ ገ/መድህን
3. አምባሳደር ብረሃነ ገ/ክርስቶስ
4. ፕ/ር ጥላሁን በየነ
5. አምባሳደር በቀለ ገለታ (ቀይ መስቀል)
6. ዶ/ር ታደሰ ወሂብ (CDC)
7. ወ/ሪት ኩለኔ ጀለታ (Uscongress) እንዲሁም ሁለት ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች ይገኙበታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.