Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ ከተማ ዙሪያ በ405 ሚሊየን ብር ወጪ የኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በመቐለ ከተማ ዙሪያ 405 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት የኤሌክትሪክ ፕሮጀክት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

ፕሮጀክቱ 25 ሺህ አባወራዎችን የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በምረቃውም የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አብርሃም በላይ÷ ” ለዓመታት በመብራት እጦት ሲቸገሩ የነበሩ ቀበሌዎች ብርሃን በመስጠታችን ላቅ ያለ ደስታ ይሰማኛል” ብለዋል።

“በህግ ማስከበር ዘመቻው የወደሙ መሰረተ-ልማቶች እየተከታተልን በመጠገን፣ አዳዲስ ተጨማሪ ፕሮጀክቶችንም እየሰራን የክልሉን ልማት እናረጋግጣለን ” ብለዋል ዋና ስራ አስፈጻሚው፡፡

ከዚህ ቀደም ተጀምረው የነበሩ ፕሮጀክቶችም በወቅቱ ለማጠናቀቅ የሚሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ዛሬ የተመረቀው ፕሮጀክትም በመጀመርያው ዙር ሰባት ቀበሌዎችን የመብራት ሃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ቀሪ ስራዎች ሲጠናቀቁም በመቐለ  ዙሪያ የሚገኙ 19 ቀበሌዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.