Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ ከተማ የሰራዊቱን የደንብ ልብስ በመልበስ ዘረፋ ላይ እየተሰማሩ ያሉ አካላትን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመቐለ ከተማ የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሳይሆኑ የሰራዊቱን የደንብ ልብስ በመልበስ ጭምር ዘረፋ ላይ እየተሰማሩ ያሉ አካላትን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡
በከተማዋ ህብረተሰቡ ሰላማዊ ኑሮ እንዳይኖር በተደራጀ ሁኔታ የፀጥታ አካላትን ልብስ በመልበስና በጦር መሳሪያ በማስፈራራት እንዲሁም የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ዝርፊያ ሲፈፀም እንደነበር የከተማው የፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ገ/እግዚአብሔር ሀይሉ ገልፀዋል፡፡
ችግሩን በማያዳግም ሁኔታ ለመፍታት የፖሊስ አባላት ቁጥር አነስተኛ መሆንና የፓትሮል ተሽከርካሪ እጥረት መኖሩን የጠቆሙት ሀላፊው÷ 1006 ወጣቶች በኮሚዩኒቲ ፓሊስነት ሰልጥነው ከፌዴራል ፓሊስ ጋር በመቀናጀት አካባቢያቸውን እየጠበቁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ማረሚያ ቤቶች አገልግሎት መስጠት ባለመጀመራቸው ተጠርጣሪዎችን ለማቆየት ችግር እንደፈጠረም ሀላፊው ተናግረው ችግሩን ለመፍታት ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር መግባባት ላይ መደረሱንም ገልጸዋል፡፡
ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት በዝርፊያ ላይ የተሰማሩ አካላትን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ በመሆኑ ችግሩ መሻሻል ማሳየቱን ጠቅሰዋል፡፡
የከተማው ነዋሪዎች በበኩላቸው÷ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ የእለት ተእለት ኑሯቸውን በሰላማዊ መንገድ መምራት መጀመራቸውን ገልፀው÷ አልፎ አልፎ በከተማዋ በዘረፋ ተግባር ላይ የሚሳተፉ አካላትን ጊዜያዊ አስተዳደሩ ለህግ እንዲያቀርብ መጠየቃቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.