Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ ከተማ ጁንታው ቀብሮት የነበረ 13 የነዳጅ ታንከር ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013(ኤፍቢሲ) በመቐለ ከተማ ልዩ ስሙ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጁንታው ለጦርነት ዓላማ ሊያውለው በድብቅ ቀብሮት የነበረ 13 የነዳጅ ታንከር ተገኘ።

በታንከሩም ከ200 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ መገኘቱ ታውቋል።

በመከላከያ ሰራዊት የ25ኛ ፈንቅል ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ ምክትል ኦፕሬሽናል አዛዥ ሻምበል ዮሐንስ ማቲዎስ እንዳስታወቁት ጁንታው ለጦርነት ዓላማ አስቦ በድብቅ ቀብሮት የነበረው 13 የነዳጅ ታንከር በመከላከያ ሰራዊቱ አሰሳ በቁጥጥር ውሏል፡፡

በታንከሩም ከ200 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

ጁንታው የትግራይ ህዝብ በነዳጅ እጥረት እንዲቸገር በማድረግ ዘርፎ ለራሱ እኩይ አላማ ቀብሮት ቆይቷል።

ሆኖም ጥቅመኛው ሃይል የደበቀው ታንከር እንዲገኝ የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ አስተዋኦ አድርጓል ብለዋል።

በአካባቢው ተቀብሮ ለነዳጅ ማጠራቀሚያ ሊውል የነበረ ተጨማሪ ዘጠኝ ታንከር መገኘቱንም ሻምበል ዮሐንስ ገልጸዋል፡፡

የህወሓት ጁንታ ለራሱ ጥቅም ብቻ የቆመ የህዝብ ጠላት መሆኑን የሚያረጋግጡ የተለያዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች እየተገኙ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

በመቐለና በተደረገው አሰሳ ለህገ ወጥ ተግባር ሊውሉ የነበሩ ቁሳቁሶች መያዛቸውንም መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.