Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ለሁለት ዓመታት ያለፍርድ ከቆዩ ተጠርጣሪዎች መካከል 614ቱ ዛሬ በዋስ ተለቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ለሁለት ዓመታት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ከቆዩ ተጠርጣሪዎች መካከል 614ቱ ዛሬ በዋስ ተለቀቁ።
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግና ፖሊስ ከግብረ ሃይሉ ጋር በመቀናጀት ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ያደረጉ ሲሆን በዚህም ፍርድ ቤት ቀርበው በተደረገው የማጣራት ሂደት 614 ተጠርጣሪዎች ዛሬ በዋስ እንዲለቀቁ ተደርጓል።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት ተጠርጣሪዎች ከዚህ በኋላ በወንጀል የሚፈለጉ ሳይሆን የልማት አርበኞች ሆነው እንዲገኙ አሳስበዋል።
የክልሉ መንግስት በመተከል ዞን ይፈጸም የነበረውን ኢሰብዓዊ ድርጊትና ሰፍኖ የነበረውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት መዋቅራዊ ለውጥ እያደረገ መሆኑንም አመልክተዋል።
በመሆኑም ዛሬ ከማረሚያ ቤት የወጡ ዜጎች በተለይ ደግሞ ወጣቶች ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ለጋራ ደህንነታቸው በቅንጅት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።
የመተከል የተቀናጀ ግብረ ሃይል አባል ብርጋዴር ጀነራል አለማየሁ ወልዴ “ወጣቶች በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው ማረሚያ ቤት መቆየታቸውን የቂም በቀል መወጣጫ ሳይሆን መማሪያ ሊያደርጉት ይገባል” ብለዋል።
ከዚህ ባለፈ በፈረሰው የህውሓት ጁንታ ኢትዮጵያን የማተራመስና የማፈራረስ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችና ቡድኖች ጋር ግንኙነት መፍጠር እንደሌለባቸው ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በተለይም መተከል እንዳትረጋጋና በሀገሪቱ ሰላም እንዳይሰፍን የሚያደርጉ ቡድኖች እንዳሉ ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ወጣቶቹ እነዚያን ሀገር አፍራሽ ቡድኖች በቃችሁ ብሎ መዋጋት እዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.