Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን አልመሃል ቀበሌ የአሸባሪው ህወሃት ሠራዊት ካምፕ ሙሉ ለሙሉ ወደመ

አዲስ አበባ፣መስከረም 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን አልመሃል ቀበሌ ልዩ ስሙ ሽንኩር መንደር የሚገኝ የአሸባሪው ህወሃት ሠራዊት ካምፕ ሙሉ ለሙሉ መውደሙ ተገለፀ፡፡

በዚህም 47 የጠላት አሸባሪዎች መደምሰሳቸውን በአካባቢው የሚገኝ ሠራዊት አመራር ሻለቃ ዮሀንስ እውነቱ ተናግረዋል ፡፡

እንደ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች ገለፃ ከሆነ በተደረገው አሰሳ የተለያዩ ጠላት ሲጠቀምባቸው የነበሩ 8 ፀረ-ተሸከርካሪ ፈንጅ እና 1 ሞቶሮላ መገናኛ ራዲዮ የተያዘ ሲሆን ÷ 2 የጠላት ሞተር ሳይክል እና የህውሃት ሠራዊት ካምፕ ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆኑ መረጋገጡን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላከክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.