Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን ከፀረ-ሠላም ኃይሎች ጋር ሲሳተፉና ሲያብሩ የነበሩ 15 ግለሰቦች በሠላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመተከል ዞን ስር በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የጸረ-ሠላም ኃይሎችን ተልዕኮ በመፈጸም ሲሳተፉ እና ሲተባበሩ የነበሩ 15 ግለሰቦች በሠላማዊ መንገድ እጃቸውን መስጠታቸው ተገለፀ፡፡
የክልሉ መንግስት ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን በዞኑ በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ ሥራዎች እየሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የፌደራልና የክልሉ የፀጥታ ኃይሎችም አካባቢውን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
በዞኑ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት በተለይም ከህብረተሰቡ ጋር እየተካሄደ ባለው ውይይትና በተደረሰው የጋራ መግባባት በወምበራ ወረዳ 14 እንዲሁም በማንዱራ ወረዳ ደግሞ አንድ ከጸረ-ሰላም ኃይሎች ጋር ሲሳተፉና ሲተባበሩ የነበሩ ግለሰቦች በሠላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጥዋል፡፡
የክልሉ መንግስት በመተከል ዞን የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሠራ ያለውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፁን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.